ማክሰኞ ፣20 ዲሴምበር 2016

አዳም ከኛ እንዳንዱ ሆነ

በሥጋው ተራክቦ ሰው እየፈጠረ፣
እስትንፋስም ጠቅሶ በህይወት አኖረ፡፡
ተመቻቸለት ምቾቱን ጨመረ፣
ለተጣሉት እንዲሁ በሳት አባረረ፣
እልህም ተጋብቶ ጥል እያከረረ፡፡
     መንገድ የራቀው ለት ሲሰራ መኪና፣
     ጐረበጠኝ ብሎ አስፋልቱን አቀና፣
     ለጥቆም መርከቡን ውሃውን ለመክፈል፣
     እንደው ምኑ ቀረው ሲፈጥር ሲፈጥር ...
በነካ እጁ ደግሞ ፍቅርንም ተማረ፣
የበደሉትንም በነፃ እየማረ፡፡
ለራባቸው ምግብ ልብስም ለታረዙት፣
ለመርዳት ሲታትር ነቅቶ በኃላፊነት፡፡
     ከኛ እንዳንዱ ሆነ የሥላሴ ስላቅ፣
     በስልጣን ላይ ስልጣን በየቀኑ ሊረቅ፣
     እንዳመነው መጠን ሲኖር የሚመረቅ፤
     እንዳመነው መጠን ሲኖር የሚመረቅ፡፡

ዓርብ ፣9 ዲሴምበር 2016

መሻቴ

መሻቴ እኔን ሽቶ፣
ፍለጋውን ለፍቶ፣
ካለሁበት መጥቶ፡፡

መኖርን ሻትኩና፣
እሱም ተገኘና፣
ፈታ ተባለና፣
ዳግም ተሰልችቶ፣
ሌላ መሻት መጥቶ፣
ደግሞ እሱም ወጥቶ፣
መጥቶ ወጥቶ፣
መጥቶ ወጥቶ …..

ዳግም ልቆ መጥቶ፣
ተገኝቶና ወጥቶ፣
እምነት ተራራ ልቤ ላይ ገንብቶ፣
ላይመለስ ሄደ ቤቴን ተሰናብቶ፡፡

ሐሙስ ፣29 ሴፕቴምበር 2016

የበሬው ስጋት