2017 ጃንዋሪ 23, ሰኞ

ዝቅታን ለመድን

እኛ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ህዝብ ነበርን፣
ዘመናዊ ትምህርት ግራ ሳያጋባን፤

የነዚ ነፃ አውጪ የነዛ ነፃ አውጪ፣
ሁልጊዜ ፍጭት ሁሌ ነገር ጠጪ፤

ጠቃሚ ሃሳብ ሲገኝ የሚሆነን ለለውጥ፣
በሰላም አንችልም ሳይሆንብን ለነውጥ፣
የተሻለ ነገር ተነግሮን አንሰማ፣
በሳት የመጣውን ክፉ ነው ስናማ

ጦርነት ደጋግሞን ዝቅ ዝቅ ሲያደርገን፣
ትውልድ ተቆጠረ ድፍን መቶ ሞላን፤
እራስን መናቁ እየደጋገመን፣
ጊዜ ቆጠረና ዝቅታን ለመድን፤

በዚ ነፃ አውጪ ዛሬም በሳት ሲለን፣
ትንሽ ነን አስባለን ዝቅታ አስለመደን፣
በወዲህም ገዢ ጫን አርጐ ሲገዛን፣
በመሃል በጭንቁ ከክር አቀጠኑን፤

ተመሳሳይ ትግል ተመሳሳይ ውጤት እየደጋገመን፣
ትንሽ ነን አስባለን ዝቅታን ለመድን፡፡

2017 ጃንዋሪ 3, ማክሰኞ

Rabi'a poem 2

Translation in Amharic by Tirsit Endeshaw

የወደድኩህ እንደው ሲኦልን ፍራቻ፣
በሳቱ አንድደኝ እንዲያው እኔን ብቻ፤

            ገነትን ፈልጌም ካልኩህ አምላኬ ሆይ፣
            ከመንግሥትህ ደስታ በፍፁም እኔን ለይ፤

ዓይኔ አንተን አንተን ሲያይ ለፍቅርህ ስርቅታ
እባክህ አትጋርደኝ ከመለኮት ደስታ፡፡

2016 ዲሴምበር 24, ቅዳሜ

Rabi'a poem

Translation in Amharic by Tirsit Endeshaw


ባንድ እጄ ውሃ ይዤ ባንዱ ነበልባል፣
ሲኦልን ላጥፋና ገነትን ላቃጥል፤

ፀሎቴ እንዳይበዛ ለገነት ጓጉቼ
አምላኬን እንዳልወድ ሲኦልን ፈርቼ፤

የነሱ ሁኔታ አይሆንህም እቻ፡፡
ፍቅርህን እንዳስብ ላንተነትህ ብቻ፡፡