2018 ጁን 26, ማክሰኞ

አገሬ አለኝ ሰው ሰው

   
      ሰው ሰው አለኝ ሃገሬ፣
     በፍቅር አጥር ታጥሬ፣
     እሙ ለአብዩ የፍቅር ገበሬ፣
     ምርጥ ዘር የዘራሽ ትላንት በሃገሬ፣
    ይኸው አበላሽን የፍቅርን ፍሬ፡፡

ህዝቡ ባንድ ተሞ ተሰብስቦ ሳየው፣
ጠረኑ አለኝ ሰው ሰው፤
አገር ማለት ሰው ነው፣
ሰው ደግሞ ፍቅር ነው፡፡

        መሪ እጅ ሲነሳኝ፣
       የሰው ክብር ሲሰጠኝ፣
       አገር ማለት ሰው ነው፣
      የሚለውን ዘፈን ልቤ እየመለሰው፣
      አገሬ አለኝ ሰው ሰው፡፡

ፍቅር የሚገደው፣
ሲያመኝ ሚጨንቀው፣
ስሞት የሚያለቅሰው፣
ወገኔን ስላየሁ፣
አገሬ አለኝ ሰው ሰው፣
ፍቅር የሚገዛው፣
ፈጣሪ ተመስገን ይህን ቀን ስላየሁ፡፡