የትርሲት ግጥሞች፡ እኔ የዕለት ሀሳቤን የምገልፅበት ግጥሞች ማስቀመጫዬ ነው፡፡ እርስዎም ለጉዋደኞችዎ እንዲያጋሩ ይበረታታሉ፡፡
ገፆች
ሳምንታዊ ግጥም
ድንቅ መጽሐፍትን በነፃ ያንቡ፡፡
ማክሰኞ 6 ሴፕቴምበር 2016
አሸንዳ
አሸንዳ
የኔ ልጅ አበባ የኔ ነጭ ወረቀት፣
በቴሌቪዥን መስኮት አይታ እንደገባት፣
ቀጤማ አገልድማ የምትጨፍርበት፣
ለአሸንዳ በዓል ባመት አደረሳት፡፡
እኔም በዚሁ መስኮት መረጃ የሰማሁት፣
የከተማው ቧንቧ ውሃ መስጠት ማቃት፣
ያሸንዳን ሌላ ገጽ ስኖር አሳየኋት፡፡
ይሄንን አሸንዳ ቅርስ ነው ያላችሁ፣
የኔን ቤት አሸንዳም አትርሱት ባካችሁ፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ
በጣም አዲስ ልጥፍ
የቆየ ልጥፍ
መነሻ
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ