ተገፊው መገፋት ልቡን አሳስኖት፣
ከፍ ወዳለው ሊሄድ ልቡ ተመኘበት፡፡
ገፊውም በፊናው 'ገፊ' ስሙን ጠልቶት፣
ዞር ሊል ተመኘ 'ገፊ' ወደማይሉት፡፡
የሰማዩ ጌታ የማይዘገይ አፍታ፣
ለማን ሰጠሁ ብሎ አይሰስት ለእፍታ፤
የየራሳቸውን ምኞት አርጐት እውነት፣
መገመት ባይችሉ አንዱ ያንዱን ፀሎት፣
እስኪያገኙት ድረስ ጓጉተው የተመኙት፣
ተገፋፍተውበት ፆሙን አሳደሩት፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ