ሰኞ 9 ጁላይ 2018

የፍቅር ነፃነት

ሁለት ጥምር ነፍሳት፣
ተራርቆ በፍርሃት፣
ሲፈነቅል ናፍቆት፣
አስመራን ጨነቃት፡፡
      የጥልን ግድግዳ፣
      በፍቅር ደርምሶት
     የክርስቶስ ክስተት፣
     ዛሬ ላይ ደገማት፡፡
የቤተሰብ ኩርፊያ፣
ተወርውሮ ወዲያ፣
በፍቅር ነፃነት፣
በታመቀ ናፍቆት፣
ኘሮቶኮል መርሳት፡፡

በፍቅር ነፃነት፣
በፈገግታ ድምቀት፣
በፍቅር ፍልቅልቅት፣
በእናቶች ቡርቅት፣
ላይመጥኑት ቃላት፣
የአስመራ ብስራት፡፡
በፍቅር መንሳፈፍ፣
በናፍቆት መንሰፍሰፍ፣
የደስታ ድምቀት፣
የይቅርታ ጥልቀት፡፡

       


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ