ማክሰኞ ፣28 ሜይ 2013

የፍቅር ሂሣብአለም ሂሣብ ሰርታ፣
ፍቅር ስጦታ፣
ባላንስ አልመጣ አለ፣
የወጣው አየለ፣
ያልተከፈለ አለ፡፡

በልቶ እንደቆሎ፣
ያልሰጠ በቶሎ፣
ፍቅርን አታለለ፣
ከአለም አጐደለ፡፡

የፍቅርን ዝውውር፣
አደረገ እንዲያጥር፣
ላለም የሾህ አጥር፣
በመሃል ጥርጥር
በጥይት ማበጠር፣
ደግሞ በድርድር፣
በነገር መካረር፡፡

ባካችሁ ልባችሁን፣
አንዴ ፈትሹልን፣
ባላንሱ ይምጣልን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ