በተስቲያን ደጅ ሄጄ ፀሎት ለማድረስ፣
እደጁ ላይ ቆምኩኝ ቅዳሴ ቢደርስ፣
ቻል እያደረኩት የልብ ወጣ ገባን፣
ለማዳመጥ ሞከርኩ ሙሉ ቅዳሴውን፣
የጌታን ቅዳሴ ሳስተውለው ለካ፣
የአጠራራችንን ሁኔታ ትረካ፣
በሰጠው ልክ ነው ሰውነት ሚለካ፡፡
ማግኘቱ አልነበረም የአብርሃም ክብሩ፣
አልተለካበትም በነበረው ብሩ፣
ቆንጥሮ የሰጠው ለእንግዳ ያለው፣
ድሃንም አግኝቶ የመፀወተው፣
በአምላኩ ሚዛን ፍፁም አከበረው፡፡
ለካስ ለነፍስ ጥቅሙዋ መስጠት ቢሰጠኝ ነው፣
የቅዳሴው ጣዕም ፀሎቴን ቀየረው፣
መስጠት እንዲሰጠኝ ጌታን ልለምነው፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ