ዓርብ ፣2 ኦገስት 2013

ደጉና ጉረኛው

ደጉና ጉረኛው ተምታቱብኝና፣
ለመለየት ብዬ ጀመርኩኝ ብተና፡፡

እንኩ ብሉ ብሉ፣
ብትጠግቡም ጨምሩ፣
በላዩም ላይ ጠጡ፣
ማህበሬን አውጡ፣
በደንብ ተቀናጡ፡፡

አጃቢ እንዳያጣ፣
ለብቻው እንዳይወጣ፣
ለራሱ ጊዜ የለው፣

እንደው ሚበትነው፣
ለሚያካብበው፣
ደግነቱ ለሰው፣
ሰጥቶ እማይደመው፡፡

ዋጋውን ምስጋና፣
ተቀብሏልና፣
ሌላውን ሽቀላ፣
ተክቶታልና፣
ልዩነቱን እንጃ፡፡

ሌላው ደሞ ደጉ
ከሁሉ ሰው እኩል፣
ለመስጠት አይቸኩል፣
ቢሰጥ ለቸገረው
ቆርሶ ከሚጐርሰው
ደብቆ ከግራው፣
ምስጋና ሳያምረው፣
ለሰው የሚደንቀው፣
አይታይ ሲደማው፣
ሰው ሁሉ የሚያማው፡፡

ደጉና ጉረኛው፣
አንድነት አላቸው፣
ሁለቱም በጃቸው፣
መስጠት አለላቸው፣
የት ሄደ ዋጋቸው፣
ለየቅል ይምራቸው፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ