ሐሙስ ፣29 ሴፕቴምበር 2016

የበሬው ስጋት


የእርሻው ዋና ተዋናይ፣
በጉልበቴ አገልጋይ፣
ሲታጨድም የማበራይ፣
ላሳዳሪዬ አለሁኝ ባይ፡፡

ልቤ ባይሞላም እኖራለሁ፣
ሰርግ ሲኖረው እየፈራሁ፣
በዓል ሲደርስም እየሰጋሁ፣
ሲዳብሰኝ ወይም ወዶኝ፣
እሰጋለሁ እንዳያርደኝ፣
ስጋዬን እንዳይዘነጣጥለኝ፣
ለደስታው እየጨነቀኝ፣
ምናለበት ወይ ቢወልደኝ፣
ለሁልቀን እንዲወደኝ፡፡

በፍቅሩ ልቤን እንዳ 'ላርቅ፣
ከኔ የጣፈጠ ምግብ አያውቅ፣
በደስታው እያልኩኝ ስቅቅ፣
በሰጠኝ ሳር ሆዴን ስልጥቅ፡፡

ምናለበት ወይ ቢወልደኝ፣
ለሁልቀን እንዲወደኝ፣
በደስታውም ደስ እንዲለኝ፣
ለህይወቴ በተዋሰኝ፤

ምናለበት ወይ ቢወልደኝ፣
ለሁልቀን እንዲወደኝ
በደስታውም ደስ እንዲለኝ፣
ለህይወቴ በተዋሰኝ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ