ማክሰኞ 9 ጁላይ 2013

ይሄም ይጋባል

በፍቅር ኑሮ ውስጥ ሲመጣ ፈተና፣
አንዱን ያሳምራል ሌላውን ሊያስቀና፣
አልያም የተወራ የሌላው ፈተና፣
ለሰማው በፊናው ጥያቄ ይፈጥርና፣
ነገሩን ያጋባል በንፋስ ጐዳና፡፡

ስንቱ ቤት ታምሷል በጐረቤት ፍቺ፣
ጥርጥር ተፈጥሯል በሌላው አምታቺ፣
ልብ ብለው ካላዩት የአይምሮን መንገድ
ልብ ውስጥ ሰርጐ ይገባል በባዶ መናደድ፡፡

ልቦች ተባበሩ ፍቅር ላይ አትክፉ፣
ፍቅርን ወላፈን አብሮ እንዳታጠፉ፡፡

የኑሮ ትክክል በሂሣብ ላይገኝ፣
ትዳራችን ላይ አንባባል እኝ-እኝ፡፡
ይልቅ የሰው ኑሮ ማየት ምን ያደርጋል፣
የነገር በሽታ በአይንም ይጋባል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ