ዓርብ ፣12 ኤፕሪል 2013

ቆንጆ ሁኚ


ቆንጆ ሁኚ እህቴ በደንብ ተዋቢ፣
ፈገግታም ጨምሪ በዛም ላይ ተግባቢ፣
በትርፍ ሰዓትሽ መጽሐፍት አንብቢ
ደስታና ፍቅርን ለራስሽ መግቢ፡፡
ትምህርትም ቢኖርሽ በራስ መተማመን፣
መናገር ብትችይም ልቀሽም ማሳመን፣
በጣም ብታነቢ ዕውቀትሽ ቢሰፋ፣
አልፈሽም ብትጽፊ ድርሰትም አንጋፋ፣
የሰው ፊት ታፍሪያለሽ ለመውጣት በይፋ፡፡
ቆንጆ ሁኚ እህቴ ይሁን ጊዜም ቢወስድ፣
የሌላው ፍቅር አለው እራሱን ለሚወድ፣
ትዳርም ልጆችም ቆንጆ ይወዳሉ፣
ጊዜ እንኳን ቢያንስሽ ቆርሰው ይበላሉ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ