ዓርብ 29 ማርች 2013

የደስታ ምንጩ

ለመማር ጓጉቼ እድሉ ተሰጠኝ፣
ሥራና ትዳርም ተባርኮ ተሰጠኝ፣
ፍሬዎችም እንዲሁ እንደጠየኩ ሰጠኝ፣
ገንዘብም ሞላልኝ ለኑሮ የሚበቃኝ፣
ስንቱን ጨቀጨኩት የደስታ ምንጭ መስሎኝ፡፡

ውጪው የታየ ለት ከኑሮ ብዥታ፣
ወጣ ብለው ካዩት ከአለም ጉብታ፣
በተሰጠን ጥቂት ትልቁ እርካታ
ለካስ ለብቻው ነው መፈንጠዝ በደስታ፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ