ዓርብ 5 ኤፕሪል 2013

ጥርጥር


ፀሐዩ ከበራ ውንትፍ ድምቅ ካለ፣
ሰማዩንም ባየው ደመና ከሌለ፣
ልጠረጥር ይሆን እህል እንደሌለ?

ኧረ በጣም ያማል አንተን መጠርጠር፣
እያየሁ በየቀን ተአምር ስትፈጥር፡፡
ጠርቼህ ሳልጨርስ  "አቤት ልጄ" የምትል፣
በወጀብ በአውሎ ውስጥ ፍፁም የምትከልል!

ዶፍ ወርዶብኝ ሳለ ጫፌን ያልነካኝ፣
ከልሎኝ ነው እኮ አንተ የወደድከኝ፡፡
 ጌታ ፍፁም ሀያል ጌታ ፍፁም ፍቅር፣
ልቤን ከልክልልኝ አንተን መጠራጠር፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ