ማክሰኞ ፣21 ሜይ 2013

ግጥም ገጠመኝ


ግጥም ገጠመኝ፣
እንድጽፍ ጠየቀኝ፡፡
ገጣሚስ አልነበርኩ፣
በየለት የታተርኩ፣
ፀሀፊም አይደለሁ፣
የተባልኩኝ አለሁ፡፡

ብቻ ባጋጠመኝ፣
እራሱ ገጠመኝ፣
በፍቅር ጠየቀኝ፣
ለመነኝ ቢያምረው፡፡

እሱ መርጦ ለጠየኝ፣
እምቢ ምለው እኔ ማነኝ?
መመረጤን እንዳልሽረው፣
ፈቀድኩለት ልጫጭረው፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ