በነገር በወሬ ጊዜ አባከኑብን፣
"የነካችሁ እንደው" ብለውም ዛቱብን፣
ጭራሽ ብሶባቸው በነገር ጐሰሙን፡፡
ትብብር ትብብር ፍቅርን በፈለግን፣
ይበቃል አይዟችሁ አትፍሩ እንዳላልን፣
በአያቶቻቸው ቃል ደግመው አስቀየሙን፡፡
ዋ ብሏል መሪያችን ተናግሯል በዛቻ፣
ዛሬ ብሩህ ቀን ነው እንሁን አቻ ለአቻ፣
ኋላ ግን የግብፅ ህዝብ ተጠንቀቅ ብያለሁ፣
ህዝቤን ተለማመጥ ተው እንዳታስቆጣው፣
የእግሩን ልቅላቂ ነው እኮ የምትጠጣው፡፡
ቅኝ ተገዝተን አናውቅ በአያቶቻችን ደም፣
ወይ አንሸነፍም ጦርነትም ብንገጥም፣
ቅንነት ደግነት ትዕግስት ያበዛነው፣
ውሃ ከምድር ሣይሆን ምንጩ ከሰማይ ነው፡፡
ግና ብሶባችሁ ጦር ቢሆን ምርጫችሁ፣
አንድ ወር ነው የሚፈጀው እንድንጨርሳችሁ፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ