ረቡዕ 27 ፌብሩዋሪ 2019

አድዋ

ምንልክ ታመሙ እጅግም ደከሙ፣
በጣም ብዙ ቀናት አልጋ ላይ ከረሙ፡፡
     ማን መጣ ጠይቀው ጣልያን ቢሏቸው፣
     ይኼ ሁሉ ህመም ባንዴ ለቀቃቸው፣
     የጣልያን ወረራ ጥቃት ባሰባቸው፡፡
ኢትዮጵያዬ ብለው በአዋጅ ድምጽ ተሳሩ፣
ሁሉም በአደ ተሞ አድዋ አደሩ፡፡
     በወርሃ የካቲት በኩዳዴ ፆሙ፣
     የጣልያንን ትዕቢት ባንዴ ከረከሙ፡፡!
አድዋ በስቃይ እጅጉን ተጨንቃ፣
እናቶች ሲያለቅሱ መቀነት አጥብቃ፣
የካቲትንን ስታልፍ በደም ተጨማልቃ፣
ከንቱ አልቀረችም የአፍሪካን ነፃነት በአንድ እጅዋ ፈንጥቃ፡፡

ሰኞ 24 ዲሴምበር 2018

በዘር ጭቃ ቦካ

የአመራር ጥበብ ረቂቅ አስተሳሰብ፣
በልጆችሽ ሃሳብ በየለቱ ሲጠብ፣
የፈላስፎች ሳይንስ ድንቁ ፖለቲካ፣
ጦቢያ ባንቺ ቤት በዘር ጭቃ ቦካ፣
ታዲያ የጨዋ ልጅ እንዴት እርሙን ይንካ!


እጀ ጠባብ ነበር ሱሪ እንኩዋን ስንጠፋ፣
ከታች ጠበብ ብሎ ወደላይ የሰፋ፣
ወይም ቀሚስ ሽንሽን በደንብ የተስፋፋ፡፡

ስልጡን ነው እያልን ለመድን መጥበቡን፣
እጀ ጠባብ ትተን ሙሉ ጠባብ ለመድን፣
አልፈንም በታይቱ እጅጉን ተጣበቅን፡፡

ጠባብ ፋሽን ሲሆን የልብሱስ ባልከፋ፣
ሃሳብ ሲጠብ ግን እጅጉን ከረፋ፡፡

ያፈርሽ ሰው ሆኜ  ጦቢያ እናት አለም፣
ለኔስ አይቀለኝም መልመድ ሌላ አለም፤
አስም አስይዞኛል ጠረንሽ ከርፍቶ፣
ሊገለኝ ይችላል አልፎ ልቤን ጐድቶ፡፡

ለእስራኤል ያልበጀ ዘሬ ዘሬ ማለት፣
ጥላቻ እየዘሩ በትጋት መኮትኮት፣
ጊዜውን ጠብቆ ፍሬውን ለመጋት፣
በየ50 ዓመቱ በጅምላ ለመሞት፡፡

የአመራር ጥበብ ረቂቅ አስተሳሰብ፣
በልጆችሽ ሃሳብ በየለቱ ሲጠብ፣
የፈላስፎች ሳይንስ ድንቁ ፖለቲካ፣
ጦቢያ ባንቺ ቤት በዘር ጭቃ ቦካ፣
ታዲያ የጨዋ ልጅ እንዴት እርሙን ይንካ!

ሐሙስ 2 ኦገስት 2018

ምስጋና ዘፍልሰታ 2010

አብይ ፆም ስንፆም እጅግ ተጨንቀን፣
አብዝተን ስናለቅስ ሽተን ሰላምን፣
አብይ የተባለ ነብይ ተሰጠን፣
በየቀኑ ፍቅር የሚያስተምረን
በመቶ ቀናት ውስጥ መቶ እርቅ አየን፡፡

አባ አባታችን ቅዱስነትዎ፣
እርቀውን ከርመው ናፍቆን ቡራኬዎ፣
እግዜር በራሱ ቀን ላገሮ አበቃዎ፤
እርቁን ተቀበሉት አብዩ እንዳይደክመው፣
መሪውን ያዝ አርጐ ነዳጅ እንዲሰጠው፡፡

አገር ግን ይገርማል ልብ ላይ ስሜቱ፣
መሶብ እንደሞላ የእንጀራ ብዛቱ፣
ማዲጋ እንደሞላ ኩሽና ዘይቱ፣
አገር ግን ይገርማል ልብ ላይ ስሜቱ፣
የጐደለው ኢምንት መስሎ መታየቱ፣
በደስታ በሰላም በጥቂት መርካቱ፣
አገር እንደዚህ ነው ሲሰጥ በረከቱ፡፡

የፍልሰታዋ ፆም እጅጉን ልዩ ነው፣
ቤትህ እርቅ ገብቷል ሁሉ ልብ አንድ ነው፣
ፀሎታችን ፍሬው ብዙው ምስጋና ነው፣
ሰው ሌላ ምን ይሻል አገር ከተሰጠው?
ሰው ሌላ ምን ይሻል አገር ከተሰጠው?

ዓርብ 27 ጁላይ 2018

ስመኘው በቀለ

የመረጥኩትን ዘር ወጥኜ ዘርቼ፣
ስመኘው በቀለ አረሙን አንስቼ፣
ልቤ እየፈካ መብቀሉን አይቼ፣
ቀድመው ቀነጠሱት ለፍሬው ጓጉቼ፡፡

ፍትህን አሳዩዋት

አብዩ ነብዩ ፍርድ ጐደለበት፣
በሰላሙ ምድር ጀግና እየሞተበት፣
ባደባባይ ካሣ ደግሞ ተሰዋበት፡፡

የደህንነት ሲመት የተቀበላችሁ፣
ለስመኝ አንድ ሺ የቀን ጅብ ይዛችሁ፣
ፍትህን አሳዩዋት ዛሬ ላገራችሁ፣
ይህን ሳትፈጽሙ እንቅልፍ አይጣላችሁ፡፡

ሰኞ 9 ጁላይ 2018

የፍቅር ነፃነት

ሁለት ጥምር ነፍሳት፣
ተራርቆ በፍርሃት፣
ሲፈነቅል ናፍቆት፣
አስመራን ጨነቃት፡፡
      የጥልን ግድግዳ፣
      በፍቅር ደርምሶት
     የክርስቶስ ክስተት፣
     ዛሬ ላይ ደገማት፡፡
የቤተሰብ ኩርፊያ፣
ተወርውሮ ወዲያ፣
በፍቅር ነፃነት፣
በታመቀ ናፍቆት፣
ኘሮቶኮል መርሳት፡፡

በፍቅር ነፃነት፣
በፈገግታ ድምቀት፣
በፍቅር ፍልቅልቅት፣
በእናቶች ቡርቅት፣
ላይመጥኑት ቃላት፣
የአስመራ ብስራት፡፡
በፍቅር መንሳፈፍ፣
በናፍቆት መንሰፍሰፍ፣
የደስታ ድምቀት፣
የይቅርታ ጥልቀት፡፡

       


ማክሰኞ 26 ጁን 2018

አገሬ አለኝ ሰው ሰው

   
      ሰው ሰው አለኝ ሃገሬ፣
     በፍቅር አጥር ታጥሬ፣
     እሙ ለአብዩ የፍቅር ገበሬ፣
     ምርጥ ዘር የዘራሽ ትላንት በሃገሬ፣
    ይኸው አበላሽን የፍቅርን ፍሬ፡፡

ህዝቡ ባንድ ተሞ ተሰብስቦ ሳየው፣
ጠረኑ አለኝ ሰው ሰው፤
አገር ማለት ሰው ነው፣
ሰው ደግሞ ፍቅር ነው፡፡

        መሪ እጅ ሲነሳኝ፣
       የሰው ክብር ሲሰጠኝ፣
       አገር ማለት ሰው ነው፣
      የሚለውን ዘፈን ልቤ እየመለሰው፣
      አገሬ አለኝ ሰው ሰው፡፡

ፍቅር የሚገደው፣
ሲያመኝ ሚጨንቀው፣
ስሞት የሚያለቅሰው፣
ወገኔን ስላየሁ፣
አገሬ አለኝ ሰው ሰው፣
ፍቅር የሚገዛው፣
ፈጣሪ ተመስገን ይህን ቀን ስላየሁ፡፡


     

ዓርብ 10 ኖቬምበር 2017

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 7

አንድ ቀን ማለዳ ባታክልቱ ቦታ፣
አበባዋን ቀጠፍኩ ብማረክ በውበቷ፤
        ያታክልቱ ጌታ ድንገት ቢመጣብኝ፣
        ክው ብርግግ ብዬ እዛው ደረቅሁኝ፣
        እርሱም ረጋ ብሎ እንዲህ ጠየቀኝ፤
"ያታክልቱ  ቦታ ሁሉ ያንተ ሳለ፣
ምነው ላንድ አበባ ልብህ ተታለለ?"


One early morning in the garden I picked a flower
the Gardener suddenly appeared and I panicked.
"Why worry about a flower, when I have
given you the entire Garden!"

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 6

ቤት ሥራ ብትልህ ነፍስህ ለመዝለቂያ፣
ቀለል አርገህ ሰራህ የዶሮ መቆያ፤
           ግመል እንዳትጋብዝ ደግሞ ተደናብረህ፣
           አይሆንም አይበቃም ትንሽ ነው ለነፍስህ፤
ሃሳብህ ዶሮ ነው ቤቱ ሰውነትህ፣
ግዙፉ ግመል ግን ያምላክ ቁራጭ ነፍስህ፡፡

Having built a hen house by yourself
do not invite a camel in!
The Hen house is your body,
the hen is your intellect, and the camel
is love's majesty in all its glory.

ሐሙስ 2 ኖቬምበር 2017

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 5

ነጠላ ነፀብራቅ ካንተ የሰረቅሁት፣
በነግ አገኘሁት ዓይኔን ቦግ አድርጐት፡፡
           ከአፍህ የወጣች ብሰማት አንዲት ቃል፣
           ላለም ደንቆሮ ሆንኩ ለህይወት ይበቃል፡፡
ግና ወንድሞቼ እንዲህ ያልተሰማችሁ፣
ካለም ተጣብቃችሁ ወየው መክረማችሁ፡፡

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 4
I stole a glance from You and my eyes
become longing and wistful.
I heard one word from Your lips and
my ears deafened to the world.

But my friend, if you have not had this experience
you are excused to be entangled in this world.

ረቡዕ 1 ኖቬምበር 2017

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 4


ፊትህን ስታዞር የርሱ ፊት በዚያ አለ፣
በመለኮት ብርሃን ማየት ለታደለ፣
የፊጣሪን ሃሳብ ምልክት ሲያይ ዋለ፡፡
             ምስጢረ መለኮት ለተገለጠለት፣
             በእንስሳት ውሎ አሊያም በዕፅዋት፣
            ፈጣሪን ያዩታልፍጥረት መስታውት
            መደነቅ መደመም በጁ ሥራ ውበት፡፡
ፈጣሪ ፍቅር ልቡ ለነደደ፣
ከጠጣው ውሃ ጋር ፍቅር ወደ ውስጡ ሄደ፣
ሌላው በውሃው ላይ የራሱን ፊት አይቶ አልፎ እየሄደ፡፡ 


Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 4


"Wherever you turn there is His face."
Those graced with clear vision see
the signs of the Creator everywhere.
For them all things, be it plant or animal,
become a contemplation of Divine beauty.
The annihilated lovers see the Beloved's face
even in the water they drink while
others only see their own reflection.

ሰኞ 9 ኦክቶበር 2017

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 3

ከኑሮ የሚበልጥ ብቸኝነት አለ፣
ከአለም የሚልቅ ነፃነትም አለ፣
ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ዋጋውም ያየለ፣
ከአምላኩ ጋራ ብቻውን የዋል፡፡


There is a loneliness more precious than life
there is a freedom more precious than the world.
Infinitely more precious than life and the world
is that moment when one is alone with God.

ሐሙስ 5 ኦክቶበር 2017

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life 2

ደስታ አልፏል ብለህ ፍፁም አትቆርቆር፣
እንዲመለስ እወቅ መልኩን በመቀየር፡፡
ወተት እሹሩሩው የህፃኑ ደስታ፣
እንዲተካ እወቅ በምግብ ጋጋታ፣
መልኩንም ቀይሮ ሲጐበኘን ደስታ፣
አንዱ ጋር ሌላ ነው ሲቀየርም ቦታ፡፡
አንድ ሰሞን ዘንቦ ሲያበሰብሰን፣
ይከተላል ደግሞ ያበባ መፍከንከን፡፡
ዛሬ ውበት ሲሆን ወይም ደግሞ እንጀራ፣
ደግሞም ይንድና ሁሉንም ተራራ፣
በፅሞና ደስታ ነፍስ ይወስዳል ተራ፡፡

በመኝታህ ሰዓት ነፍስህ ትታህ ስትሄድ፣
እራስህን ብታይ ሆነህ ረጅሙን ጽድ፣
አሊያም ፅጌረዳ በውበት የምትነድ
ወንድሜ አትሸወድ በቅዠትህ መውደድ፣
ከልብህ በስተቀር ሌላ አይምራህ መንገድ፡፡




Poem translated from Rumi’s Little Book of Life
Do not grieve over past joys, be sure
they will reappear in another form.
A child's joy is in milk and nursing
but once weaned, it finds new joy
in bread and honey.
Joy appears in many different forms
in moves from place to place.
It may suddenly show in the falling rain
or in the rose bed; it comes now as water,
now as beauty, or as nourishing bread.
But suddenly it may show its face
from behind the veil and destroy all idols
that prevent you from seeking the divine.
In sleep when the soul leaves the body
you may dream of yourself as a tall cypress
or as a beautiful rose, but be warned, my friend,
all these phantoms dissolve into thin air
once the soul returns to the body.
Do not rely on anything but your heart.

ረቡዕ 4 ኦክቶበር 2017

Poem translated from Rumi’s Little Book of Life

የመጣንበትን ክብር በመዘንጋት፣
ብልጭልጩን አይተን ወደሱ በመትጋት፤
እጅጉን ይደንቃል እንዲህ ዋጋ ማጣት፣
ላለም ምናምንቴ ነፍሣችንን መስጠት፡፡



Indulging our pride, we run after
Every fleeting image.
How odd that being so unimportant

We cultivate such grand illusions.

ዓርብ 8 ሴፕቴምበር 2017

ፍልስፍና - ዘመድህ አድርገኝ

የዘርዐ ያዕቆብን ፍልስፍና የሚል መጽሐፍ አንብቤ እንደው የነካኝን ማንነቱን የፍቅር መምህርነቱን ከዚህ ትውልድ ጋር እንዲህ አገናዝቤ ከተብኩት፡፡

ዘርዓያዕቆብ ዘረ ስደተኛ፣
እምነት ፍቅር አንሶት ከሆነ ጦረኛ፣
ዘመዶችህን ተውህ ለክፋት ላትተኛ፤
በዋሻ ተደበቅህ ክፉ ቀን እስኪያልፍ፣
ብዙ ኑሮህን ኖርህ በፈጣሪ እቅፍ፡፡

           ጵጵስና ታጨተህ በዋሻ ውስጥ ብትቆይ፣
           ቤተስቲያን ልትኖር የግዚአብሔር አገልጋይ፣
           መቼ አወቁልህ በሰው ናፍቆት ብትጋይ፣
           ነገርን ለመሸሽ ከመንጋው ብትለይ፣
           ከጥላቻ እንጂ ከሰው እንዳትለይ፡፡

 ደግሞም የተጠጋህ ከሃብቱ በሥራ፣
 ለኑሮ የሚበቃ መሆን መረጥህ ተራ፣
 የሃብቱን ደግነት እጅጉን መረጥኸው፣
 የሚልቅን ዋጋ ዝምድናን ጠየቅኸው፡፡
በሃብቱ ዝምድናም እጅጉን ተባረክህ፣
ጐረቤቱም ሆነህ ፍቅር ቤትህን ሰራህ
ዘመዶችህንም በፍቅር ተሰናበትህ፡፡

      ያንተ አርዓያ ዘሩ በርክቶ በዛና፣
      ሁሉም ዘመዶቹን እጅጉን ተወና፣
     ስደትን መረጠ እርቆ ወጣና፡፡

እድሉን ቢሰጠው ሰርቶ እንዲበላ፣
እየተዘመደ ባለም ሁሉ መላ፡፡

ማክሰኞ 5 ሴፕቴምበር 2017

ጉም

ይሄ ጉም ምንድነው እንዲህ የተቀናጣ፣
እንደ ፍልቅቁ ጥጥ ፍሬው እንደወጣ፣
ንጥት ጽድት ብሎ በራሱ ቅርጽ ወጣ፡፡


               ወንድምየው ውሃ ያለቅርጽ የወጣ፣
               ይሄ የመሬት ስበት እንዲህ ቅጥ ካሳጣ፣
              ይሄ ካፈር መኖር ጣጣውን ስንወጣ፣
              እኛስ እንዴት እንሆን ወደላይ ስልወጣ?

ሐሙስ 8 ጁን 2017

ለዲቃላው ልጄ

ለዲቃላው ልጄ
አንድ በስልሣዎቹ መጨረሻ አካባቢ የሚገኙ ጐልማሣ ታሪክ ነው፡፡ በትዳራቸው ብዙ አመት የኖሩ ነገር ግን በትዳራቸው ልጅ ስላልነበራቸው ለእሳቸው በገባቸው መንገድ ምስታቸውንም ሳያስቀይሙ የልጅ አምሮታቸውን በድብቅ ወልደው በድብቅ አሳድገው የተወጡ ሰው ናቸው፡፡ የልጃቸውን ንዴት የእሳቸውን እርካታ ታሪክ ሰምቼ ታሪካቸውንና የእሳቸውን ስሜት እንዲህ ከተብኩት፡፡
ከቤቴ አጥቼህ ከውጭ ያገኘሁህ፣
ሙሉ ሰው እያለህ ዲቃላ ያስባልኩህ፤
አዎን ውዴ አለሜ አንተ ያጥንቴ ፍላጭ፣
አዎን የኔ ጌታ አንተ የደሜ ምጣጭ፣
እውነት ነው መውደዴ እራሴን አብዝቼ፣
እንደምሞት ሳስብ መጥፋትን ፈርቼ፣
ከተከበርኩበት ክብር ተፈትቼ፣
አንተን የወለድኩህ ትክክልን ትቼ፣
የልጅነት ፍቅሬን እምነቴን ጐድቼ፣
የግራዋን ጐኔን አንገት አስደፍቼ፡፡

አውቃለሁ አለሜ ይቅር እንዳትለኝ፣
ለኔ ግን ስህተቴ ፍፁም አይሰማኝ፣
አይንህን እያየሁ መኖር ስለሚሰማኝ፤
በልጅነትህ ውስጥ ሁሌ እታደሳለሁ፣
ህይወቴ ሲቀጥል ባንተ ውስጥ አያለሁ፡፡

አዎን ውዴ አለሜ አጥፍቻለሁ በጣም፣
ግና፣ … ዛሬ ላይም ሆኜ ወደኋላ ሳስብ፣
አንተን እያየሁኝ እኔ አልፀፀትም፤
ታዲያ አጠፋሁ ብዬ ልቤ ሳይፀፀት፣
ይቅርታ እንዳልል ሆኖብኛል ምፀት፡፡

እናም የኔ ጌታ የህይወቴ ቅጣይ፣
እድሜ ይስጠንና አንተም አይንህን እይ፡፡